ሲበሉ የላኩት
ምሳውን ሲበላ አሽከሩን ላከው፡፡ የተላከ አፉን ላከከ እንደሚባለው ቢያጐርሰው እኮ በተሻለው ነበር፡፡ አሽከሩ
ሲላክ ያይ የነበረው ከጌታው ፊት የቀረበውን መብል እንጂ የጌታውን መልዕክት አልነበረም፡፡ የሆድ ነገር ሆድ
ይበላልና፣ የምግቡን ጉምጃን ብቻ በሆዱ ሲያጢያጢን፤ መንገድ ቢጀምር ምን እንደተላከና ወዴት እንደተላከ መልዕክቱንም
የተላከበትንም አንዱንም አጣው፡፡
መመለስ አይቀርምና የማታ ማታ ወደጌታው ተመለሰና፣ ጌታው እህ ቢለው ምን እህ አለ፣ አጉርሰው ልከውኝ ቢሆን፣
የእኔም ልብ ባልጠፋም፣ የርስዎም መልዕክት ባልተጓጐለም ነበር ብሎ ሲበላ የላከውን መልዕክት አደረሰ፡፡
No comments:
Post a Comment